Featured Post

10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer

Image
  10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer 1. ሁላችንም የጥቃት ዒላማ ውስጥ መሆናችንን መረዳት መቼም ቢሆን “የሳይበር ጥቃት እኔን አያጋጥመኝም" ብሎ አለማሰብ፡፡ ሁላችንም በግል እና በምናደርጋቸው የገንዘብ ዝውውሮች እንቅስቃሴያችን ወይም በነበረን መልካም ስም ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር አደጋ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሁሉም ሰው ኃላፊነት ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 2. ለሶፍትዌሮች ወቅታዊ ዝመና ያድርጉ የኦፕሬቲንግ ሲስተሞቻችን /Operating System/ እና ፕሮግራሞቻችን የዘመኑ ሶፍትዌሮችን መጫን መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜም የቅርብ ምርት የሆኑ የደህንነት ዝመናዎችን ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም፡- • የመሣሪያዎትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ቀጥተኛ ዝመና /Automatic Update/ ላይ ያድረጉ፣ • ቀጥተኛ የደህንነት ዝመና በየጊዜው የሚያቀርቡ እንደ ክሮም ወይም ፋየር ፎክስ /Chrome or Firefox/ ያሉ የድረ-ገጽ ማፈላለጊያዎችን መጠቀም ይመከራል፣ • እንደ ፍላሽ፣ ሀርድ ዲስክ እና የመሳሰሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን ሲጠቀሙ ሁልጊዜም ወቅታዊ ዝመና የተደረገላቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ 3. የፌሺንግ ጥቃት ሙከራዎችን ያስወግዱ የፊሺንግ ጥቃት የተለያዩ የማህበራዊ ምህንድስና መንገዶችን በመጠቀም የሚፈፀም ቋሚ ስጋት ሲሆን የሳይበር ወንጀሎች እንደ የይለፍ ቃል ባንክ መረጃዎች እና ክሬዲት ካርድ ያሉ ግላዊ መረጃዎችን የሚያጭበረብሩበት ነው፡፡ • የፊሺንግ ጥቃት ብዙውን ጊዜ በኢ-ሜይል አድራሻ፣ ከዚህ በተጨማሪም በስልክ፣ በመልዕክት መለዋወጫ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የሚፈጸ...

#ለመሆኑ_ኢንተርኔትን የሚቆጣጠረው ማነው? Who Controls The INTERNET?

እነዚህ በተለያየ የአለም ክፍል የሚኖሩ ሰዎች ይህን የሚፈጽሙት በከፍተኛ ሚስጥር የተያዙ ሰባት የቁልፍ ቁጥሮችን በተናጠል በ 3 ወር እየተቀያየሩ በመያዝ ነው። ይህ ከሳይንስ ፊክሽን ላይ የተወሰደ ታሪክ እንጂ እውነት ላይመስል ይችላል።
"Crypto officers" በሚል ስም የሚጠሩት እነዚህ14 ግለሰቦች "internet corporation for assigned names and numbers (ICANN) የሚባል ለድረ ገጾች የ IP አድራሻ ሰውኛ ትርጉም ያለው አድራሻ የሚሰጥና የማስተደደር ስልጣን ያለው ተቋም አባላት ሲሆኑ ዋና ኋላፊነታቸውም የ Domain name system (DNS) አሰራርን የሚያስተናግዱ የኮምፕዩተር ሰርቨሮችን በከፍተኛ ደረጃ ምንም እክል እንዳይገጥማቸው መጠበቅ ነው።
በኦክቶበር 2016 ዲን በተሰኘ ኩባንያ ላይ በሀከሮች በተሰነዘረ ጥቃት አማዞንን እና ትዊተርን ጨምሮ በርካታ ድረ ገጾች ጥቃት ደርሶባቸው ለደቂቃዎች ተቋርጠው ነበር። ዲን የ DNS አገልግሎትን ከሚሰጡ ተቋማት ውስጥ ተቀዳሚው ነው።
የDNS አሰራር ዋና ተግባር በሰው ጭንቅላት መነበብ የሚችልን (ለምሳሌ www.amazon.com) የድረገጽ አድራሻ በኮምፒዩተር መነበብ ወደ ሚችል (ለምሳሌ http፡//173.252.110.27) የ Ip አድራሻ መቀየር ነው። ይህ አሰራር ባይኖር ኖሮ እያንዳንዷን ለመጠቀም የምንፈልገውን ድረገጽ ከላይ በተጠቀሰው አይነት የ IP አድራሻ አስታውሰን መጠቀም ይኖርብን ነበር።
ሀከሮች ተሳክቶላቸው የዲን ኩባንያን ባጠቁበት መንገድ የ ICANN ቤተመረጃ ሰብረው መግባት ቢችሉ በአጠቃላይ የአለምን የኢንተርኔት አሰራር መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ ሰዎችን ትክክለኛ ወዳልሆነና ገንዘባቸውን ሊያዘርፋቸው ወደሚችል የባንክ መሳይ ድረገጽ አታለው ሊወስዷቸው ይችላል።
ለዚህም ነው ይህ ከፍተኛ ጥበቃ የሚያስፈልገው የ DNS server አንድ ሰው ብቻ እንዲቆጣጠረው ላለማድረግ ሰባት ሰዎች ለየብቻ በሚይዙት ልዩ የሚስጥር ኮድ ተቆልፎ አንድ ላይ ተገናኝተው በአንድነት ሲያቀናብሩት ብቻ መስራት በሚችል አሰራር ይጠበቃል። ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ በተጠባባቂነት የተመረጡ የሚስጥር ቁልፎች ተሰጥቷቸው በተጠባባቂነት ይቆያሉ!
ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!
📌ውድ የቻናላችን ተከታታዮች መረጃዎችን በ "video" መከታተል ለምትፈልጉ የ youtube ቻናላችንን ከታች ባለው ሊንክ ገብታችው Subscribe በማድረግ መከታተል ትችላላችሁ።

Comments

Popular posts from this blog

WHO IS FULL-STACK DEVELOPER & WHY MANY PROGRAMMERS FAIL?

10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer

Top 5 Ways To Protect You From Hackers Online 2020 Tips