Featured Post

10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer

 10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer



1. ሁላችንም የጥቃት ዒላማ ውስጥ መሆናችንን መረዳት

መቼም ቢሆን “የሳይበር ጥቃት እኔን አያጋጥመኝም" ብሎ አለማሰብ፡፡ ሁላችንም በግል እና በምናደርጋቸው የገንዘብ ዝውውሮች እንቅስቃሴያችን ወይም በነበረን መልካም ስም ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር አደጋ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሁሉም ሰው ኃላፊነት ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

2. ለሶፍትዌሮች ወቅታዊ ዝመና ያድርጉ

የኦፕሬቲንግ ሲስተሞቻችን /Operating System/ እና ፕሮግራሞቻችን የዘመኑ ሶፍትዌሮችን መጫን መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜም የቅርብ ምርት የሆኑ የደህንነት ዝመናዎችን ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም፡-

• የመሣሪያዎትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ቀጥተኛ ዝመና /Automatic Update/ ላይ ያድረጉ፣

• ቀጥተኛ የደህንነት ዝመና በየጊዜው የሚያቀርቡ እንደ ክሮም ወይም ፋየር ፎክስ /Chrome or Firefox/ ያሉ የድረ-ገጽ ማፈላለጊያዎችን መጠቀም ይመከራል፣

• እንደ ፍላሽ፣ ሀርድ ዲስክ እና የመሳሰሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን ሲጠቀሙ ሁልጊዜም ወቅታዊ ዝመና የተደረገላቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

3. የፌሺንግ ጥቃት ሙከራዎችን ያስወግዱ የፊሺንግ ጥቃት የተለያዩ የማህበራዊ ምህንድስና መንገዶችን በመጠቀም የሚፈፀም ቋሚ ስጋት ሲሆን የሳይበር ወንጀሎች እንደ የይለፍ ቃል ባንክ መረጃዎች እና ክሬዲት ካርድ ያሉ ግላዊ መረጃዎችን የሚያጭበረብሩበት ነው፡፡

• የፊሺንግ ጥቃት ብዙውን ጊዜ በኢ-ሜይል አድራሻ፣ ከዚህ በተጨማሪም በስልክ፣ በመልዕክት መለዋወጫ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የሚፈጸም ነው፡፡

• ማናቸውም እውነተኛ የሚመስሉ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን እና የስልክ ጥሪዎቻችን ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፤

4. ጠንካራ ይለፍ ቃል መጠቀም ለተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የምንጠቀምባቸው በርካታ የይለፍ ቃላት ሊኖሩን እና በአግባቡ መጠቀም ሊኖርብን እንችላለን፡፡ ጠንካራ የይለፍ ቃል የምንለው በቃላት በቁጥር አንዲሁም በተለያዩ ምልክቶች የተዋቀረ ሲሆን ነው፡፡ የምንጠቀማቸው የይለፍ ቃሎች ከመብዛታቸው የተነሳ አንድን የይለፍ ቃል ለበርካታ አማራጮች የምንጠቀምበት ሁኔታዎች ሁሉ ሊኖሩ ይችላል፡፡

ነገር ግን ሊያጋጥመን የሚችልን ጥቃት ለመከላከል ጠንካራ የይለፍ ቃል የመጠቀምና የማስተዳደር ልምዶችን ልናጎለብት ይገባል፡፡

5. የምንከፍታቸው ድረ-ገጾች እና አባሪዎች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የማይታወቁ ድረ-ገጾችን ከመመልከት እና ሶፍትዌሮችን ከማይታመኑ ምንጮች ከማውረድ መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ እንደዚህ አይነት ገጾች አጥፊ ሶፍትዌሮችን የያዙ በመሆናቸው በፍጥነት በኮምፒውተር ስርዓቶቻችን ላይ በመጫን ጉዳት ያስከትላሉ፡፡ ስለዚህ በኢ-ሜይል የሚላኩልንን አባሪ ወይም ማስፈንጠሪያዎች ያልተለመዱ እና አጠራጣሪ ከመሰሉን ከመክፈት መቆጠብ ተገቢ ነው፡፡

6. መረጃ ማስቀመጫ መሣሪያዎችን በአግባቡ መያዝ ለምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች እንደውስጣዊ ደህንነት ማስጠበቂያ ሁሉ አካላዊ ጉዳት እንዳያጋጥማቸው ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

• ላፕቶፕ ኮምፒውተራችንን፣ የእጅ ስልካችንን ወይም ታብሌታችንን ለሆነ ቆይታ ከነበርንበት ስፍራ አስቀምጠን ዘወር የምንል ከሆነ አስቀድመን መሣሪያዎቹን መዘጋታቸውን መረጋገጥ ይገባል፡፡

• ምስጢራዊ መረጃዎችን በፍላሽ ወይም በሌላ ውጫዊ ተንቀሳቃሽ መረጃ መቆለፋቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡

• በዴስክቶፕ ኮምፒውተር የምንጠቀም ከሆነ በማንጠቀምበት ሰዓት ስክሪኑን መዝጋት ወይም ማጥፋት ያስፈልጋል፡፡

7. ጠቃሚና ምስጢራዊ ለሆኑ መረጃዎች ጥበቃ ማድረግ

ሁልጊዜም ጥንቃቄ ለሚሹ መረጃዎች ተገቢው ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡

• ሚስጥራዊ የሆኑ እና ጠቀሜታ ያላቸውን ግላዊ መረጃዎች አንዲሁም እንደክሬዲት ካርድ፣ የተማሪዎች ፋይል፣ የጤና ክትትል መረጃ እና የመሳሰሉትን መረጃዎች ከስራ ቦታ፣ ከላፕቶፕ እና ሞባይል ስልኮች ላይ ማስወገድ፤

• መረጃዎች የምንይዝበትን ቁሶችን በምናስወግድበት ወይም ለሌላ ሰው አሳልፈን በምንሰጥበት ወቅት ምስጢራዊ መረጃዎቹን በጥንቃቄ ማጥፋት ያስፈልጋል፡፡

• ሁልጊዜም ጥንቃቄ የሚሹ መረጃዎችን ስናከማች ወይም ስናስተላልፍ የመመስጠር ዘዴን ልንጠቀም ይገባል፡፡

8. ሞባይል ስልኮችን ደህንነት መጠበቅ

በሞባይል ስልኮቻችን መረጃን የመያዝ ልማድ ቢኖርም እነዚህ የእጅ ስልኮቻችን ለጥቃት የተጋለጡ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

• የሞባይል ስልኮችን በፍፁም ያለ የይለፍ ቃል አለመጠቀም፤

• ታማኝ ከሆኑ ምንጮች ብቻ መተግበሪያዎችን ማውረድ /Apple App Store, Google Play …/፣

• ለምንጠቀምበትን መሣሪያ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ወቅታዊ ዝመና ማድረግ፣ የሚላኩ አባሪዎችን እና መስፈንጠሪያዎችን ከመክፈት መቆጠብ፤

• ግላዊ ምስጢራዊ መረጃዎችን በሞባይል ስልኮቻችን ውስጥ ከማስቀመጥ መቆጠብ፤

• አብዛኞቹ በእጅ የሚያዙ ስልኮችን የመመስጠሪያ መንገዶች ያሉዋቸው በመሆኑ መጠቀም ተገቢ ነው፤

9. ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም

ተማኝ ከሆኑ ምንጮች የሚገኙ ፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እና ስርዓቶቻችንን በየጊዜው ማዘመን ያስፈልጋል፡፡

10. መጠባበቂያ መያዝ
በየጊዜው መጠባበቂያ ፋይል የመያዝ ባህልን ማዳበር ያስፈልጋል፡፡ ይህም ፋይሎችን የያዙ መሣሪያዎች ላይ ጉዳት ቢያጋጥም በመጠባበቂያ ያስቀመጥነውን ፋይል መልሶ ለመጠቀም ያግዛል፡፡


Follow us on YouTube Facebook

Comments

Popular posts from this blog

WHO IS FULL-STACK DEVELOPER & WHY MANY PROGRAMMERS FAIL?

Top 5 Ways To Protect You From Hackers Online 2020 Tips