Posts

Showing posts from May, 2021

Featured Post

10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer

Image
  10 መሠረታዊ የኮምፒውተሮቻችንን ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች 10 Basic Ways to Secure Your Computer 1. ሁላችንም የጥቃት ዒላማ ውስጥ መሆናችንን መረዳት መቼም ቢሆን “የሳይበር ጥቃት እኔን አያጋጥመኝም" ብሎ አለማሰብ፡፡ ሁላችንም በግል እና በምናደርጋቸው የገንዘብ ዝውውሮች እንቅስቃሴያችን ወይም በነበረን መልካም ስም ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር አደጋ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሁሉም ሰው ኃላፊነት ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ 2. ለሶፍትዌሮች ወቅታዊ ዝመና ያድርጉ የኦፕሬቲንግ ሲስተሞቻችን /Operating System/ እና ፕሮግራሞቻችን የዘመኑ ሶፍትዌሮችን መጫን መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜም የቅርብ ምርት የሆኑ የደህንነት ዝመናዎችን ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም፡- • የመሣሪያዎትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ቀጥተኛ ዝመና /Automatic Update/ ላይ ያድረጉ፣ • ቀጥተኛ የደህንነት ዝመና በየጊዜው የሚያቀርቡ እንደ ክሮም ወይም ፋየር ፎክስ /Chrome or Firefox/ ያሉ የድረ-ገጽ ማፈላለጊያዎችን መጠቀም ይመከራል፣ • እንደ ፍላሽ፣ ሀርድ ዲስክ እና የመሳሰሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን ሲጠቀሙ ሁልጊዜም ወቅታዊ ዝመና የተደረገላቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ 3. የፌሺንግ ጥቃት ሙከራዎችን ያስወግዱ የፊሺንግ ጥቃት የተለያዩ የማህበራዊ ምህንድስና መንገዶችን በመጠቀም የሚፈፀም ቋሚ ስጋት ሲሆን የሳይበር ወንጀሎች እንደ የይለፍ ቃል ባንክ መረጃዎች እና ክሬዲት ካርድ ያሉ ግላዊ መረጃዎችን የሚያጭበረብሩበት ነው፡፡ • የፊሺንግ ጥቃት ብዙውን ጊዜ በኢ-ሜይል አድራሻ፣ ከዚህ በተጨማሪም በስልክ፣ በመልዕክት መለዋወጫ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የሚፈጸ...

እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው “የራንሰምዌር” ጥቃት Ransomware attacks becoming a major concern

Image
  እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው “የራንሰምዌር” ጥቃት | Ransomware attacks becoming a major concern ከጥቂት ሳምንታንት በፊት በአሜሪካን የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈጸመ የራንሰምዌር ጥቃት ሳቢያ በሀሪቱ የነዳጅ አቅርቦት ስርዓት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል ፈጥሮ ሰንብቷል፡፡ የራንሰምዌር ጥቃቱ የአገሪቱን ትልቁን የነዳጅ ቧንቧ መስመር ከአገልግሎት ውጭ በማድረግ የአሜሪካ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ሕግ እንዲያወጣ አስገድዷል፡፡ ይህ ጥቃት በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ በርካታ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ ሲሆን ከነዚህም መካከል አቅራቢዎች በካምፓኒዎች ዘንድ ያላቸውን ተአማኒነት መልሰው ለማግኘት ረጅም ጊዜ ይወስድባቸዋል፡፡ የራንሰምዌር ጥቃቶች የሚሰነዘሩት በዋናነት በንግድ ሥራ በተሰማሩ አካላት ላይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህ የያዝነዉ የፈረንጆቹ 2021 በራንሰምዌር ጥቃት መላው ዓለም በተለይም የጤና ተቋማት ክፉኛ የተጠቁበት ዓመት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ የእነዚህ የራንሰምዌር ጥቃት አድራሾች ዋና አላማ የንግድ አገልግሎትን ማስተጓጎል ነው፡፡ ከዚህም ባለፈም ወሳኝ የሚባሉ አገልግሎት አቅራቢዎች በራንሰምዌር ጥቃት ፈጻሚዎች ዒላማ እይታ ውስጥ ናቸው ምክንያቱም በራንሰምዌር ጥቃት ሲሰነዘርባቸው ላልተወሰነ ጊዜ የንግድ ሥራ ሂደቶች ሊቋረጡ ወይም ጥቃቱን የሰነዘረው አካል ለጠየቀው የራንሰም ክፍያ ከፍለው የተቋረጠውን አገልግሎት ወደማስመለስ ግዴታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በንግድ ሥራ ዉስጥ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎትን ማቋረጥ እና መዝጋት ከፍተኛ ኪሳራን ስለሚያደርስ በአብዛኞቹ የጥቃት ሰለባዎች ዘንድ እንደመፍትሔ አይወሰድም፡፡ በመሆኑም አገልግሎት አቅራቢዎች ክፍያ ወደመፈፀም አማራጭ ብቻ ተገደው እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡ ስለ...